እግዚአብሔርን በስታዲየም መሃል ማግኘት፡ ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተማርኩት

How a busy concession stand became a cathedral of service and a testament to our community's faith

VOLUNTEER EXPERIENCE

ጸሐፊ፦ ያሬድ

2/6/20262 min read

ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን የምናገኘው በዝምታ ውስጥ ይመስለናል። በቤተክርስቲያን ጸጥታ ወይም በገዳም ርጋታ ውስጥ ፈጣሪን መፈለግ የተለመደ ነው። ነገር ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ እኔ እግዚአብሔርን ያገኘሁት ፈጽሞ ባልጠበቅሁት ቦታ ነበር—በሜሪላንድ ስታዲየም ጩኸት፣ ጭስ እና ግርግር መሃል።

የቅዱስ አማኑኤልን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዳስተባበር የተሰጠኝ ኃላፊነት፣ አንድ ትልቅ እውነትን እንድታዘብ ረድቶኛል። የቤተክርስቲያናችን ምእመናን—አባቶች፣ ዶክተሮች፣ ተማሪዎች እና እናቶች—አንድን የስታዲየም ኪዮስክ ወደ ቅዱስ የአገልግሎት ስፍራ ሲቀይሩት ተመልክቻለሁ።

መሪነት ሁልጊዜ በራስ መተማመን ብቻ አይደለም፤ ብዙውን ጊዜ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ማመንን ይጠይቃል። የፈቃደኛ ሰራተኞች ስም ዝርዝር (Roster) ባዶ ሆኖ ያየሁባቸውን ሳምንታት አልረሳቸውም። የቤተክርስቲያናችንን የብድር (Mortgage) ክፍያ የመሸፈን አደራ በትከሻዬ ላይ ሲከብደኝ፣ እንደ ሰው እጨነቅ ነበር። በእነዚያ የጭንቀት ጊዜያት ጉልበት የሆነኝ የኔ ጥበብ ሳይሆን፣ የነህምያ ቃል ነበር— "የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል" (ነህምያ 2፥20)።

እናም እግዚአብሔር ቃሉን ጠበቀ—በነዚህ ታላላቅ ሰዎች በኩል።

ከማዕረግ ይልቅ ትህትና

በዚያ በረዶ እና ሙቀት ውስጥ ተስፋ ሳልቆርጥ እንድቀጥል ያደረገኝ፣ የሽያጭ አላማው አልነበረም፤ ይልቁንም የአገልጋዮቹ መንፈስ ነበር። በውጪው ዓለም ትልቅ ደረጃ እና ክብር ያላቸው ሰዎች፣ ካባቸውን አውልቀው ሽርጥ ታጥቀው ሲሰሩ ማየት ልብን ይነካ ነበር። በፈላ ዘይት ፊት ለፊት ቆመው፣ በሙቀት እየተቃጠሉ ግን በፈገግታ የሚያገለግሉትን ወንድሞችና እህቶች ስመለከት፤ እውነተኛ ትህትና ምን እንደሆነ ተማርኩ። እግሮቻቸው እያበጠ፣ "ለቤተክርስቲያኔ ነው" ብለው ሳይቀመጡ የሚሰሩ አባቶችን አይቼ በጽናት እንድቆም አቅም አገኘሁ።

በዚያ የጋራ ድካም ውስጥ ልዩ ቤተሰብነት ተፈጠረ። በሌሊት አውቶቡስ ውስጥ፣ የወይዘሮ ኢትዮጵያን ትኩስ ቡና እየጠጣን ስንጓዝ፣ የሥራ ባልደረቦች አልነበርንም—አንድ አካል እንጂ።

የማይታዩ ምሰሶዎች

ምንም እንኳን ይህንን ቡድን የመምራት ዕድሉ ቢኖረኝም፣ የእውነተኛው ጥንካሬ ምንጭ ግን የጋራ ህብረቱ ነበር። እንደ ዮርዳኖስ፣ ቢኒ፣ ሚሊዮን፣ ዮሴፍ፣ ዶ/ር ግሩም እና አሰገደች ያሉ ወንድሞችና እህቶች፣ ራሳቸውን እንደ ተራ አገልጋይ ቆጥረው የሎጂስቲክስና የትራንስፖርት ሸክሙን ሲያቀሉልን ተመልክቻለሁ። ቤተክርስቲያን የምትቆመው በመድረክ ላይ በሚታዩት ብቻ ሳይሆን፣ እንደነዚህ ዓይነት በጓዳ በሚሰሩ ታላላቅ ምሰሶዎች መሆኑን በተግባር አስረግጠውልኛል።

ለምን ጩኸቱን ቻልን?

ለውጭ ሰው፣ በስታዲየም ሆትዶግ መሸጥ ተራ ንግድ ሊመስል ይችላል። እኛ ግን እውነቱን እናውቃለን። እኛ በዚያ የዓለም ጩኸት ውስጥ የቆምነው፣ የቅዱስ አማኑኤል ሰላም እንዳይደፈርስ ነው። እኛ የቆምነው፣ የቤተክርስቲያናችን ጉልላት በክብር ከፍ ብሎ እንዲታይ፣ እጣኑ ወደላይ እንዲወጣና ልጆቻችን የራሳቸው መመኪያ እንዲኖራቸው ነው።

እናቴ "ልብ ይመርቅ" ትል ነበር። ይህንን የተጋድሎ ዘመን ወደኋላ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ከዚህ የተሻለ መዝጊያ ቃል የለም። እንደዚህ ዓይነት እምነት ካላቸው ሰዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ ተደግፌ ማገልገሌ ለእኔ ትልቅ በረከት ነው። የእግዚአብሔርን ቤት ስንገነባ፣ እሱ ደግሞ የእኛን ቤት እንደሚገነባ አይተናልና።

God in the Bleachers: What I Learned Leading the St. Amanuel Volunteer Team


People often associate finding God with silence—the quiet of a monastery or the hush of a sanctuary. But for the past two years, I have found God in the most unexpected place: amidst the smell of frying oil and the deafening roar of a Maryland stadium.

As the lead organizer for St. Amanuel’s stadium volunteer program, I had a unique vantage point. I wasn't just managing a schedule; I was witnessing a transformation. I watched as a group of church members—elders, doctors, students, and parents—turned a concession stand into a cathedral of service.

Leadership is often painted as a role of strength, but I learned that it often starts with vulnerability. I remember specific weeks when the volunteer roster was terrifyingly empty. The responsibility of securing the funds for our church’s mortgage weighed heavily on me. In those moments of quiet panic, I didn't find comfort in spreadsheets, but in scripture. Nehemiah 2:20 became my anchor: "The God of heaven will give us success."

And He did—through them.

A Theology of the Grill

What kept me moving wasn't the goal of meeting a sales quota. It was watching the volunteers. I observed men and women who command respect in their professional lives stripping away their titles to put on black aprons. I saw "French Fry Masters" standing over boiling oil for ten hours, not with complaints, but with smiles. I saw elders standing on swollen feet, refusing to sit because they knew that every shift served a greater purpose.

There was a profound humility in that heat. On the late-night bus rides back, sharing W/ro Ethiopia’s thermos of hot coffee, the boundaries between us dissolved. We weren't just a workforce; we were a family bound by a "theology of the grill"—the belief that serving food could be a holy act if done for the love of God's house.

The Invisible Pillars

While I had the privilege of leading, the true strength came from the collective. I watched leaders like Yordanos, Bini, Million, Yoseph, Dr. Girum, and Asegdech take on burdens that weren't theirs to carry. They drove vans, managed logistics, and filled gaps without seeking recognition. They reminded me that the church isn't built by the few who stand at the pulpit, but by the many who serve in the shadows.

Why We Endured the Noise

To the outsider, it might look like we were just selling hotdogs. But inside that stand, we knew the truth. We weren't working for profit; we were working for peace. We stood in the noise of the world so that the prayers in our sanctuary could continue in silence. We worked to ensure that the incense keeps rising and the Gulelat (dome) of St. Amanuel remains high for our children.

My mother used to say, "Lib Yimerq"—"May the heart itself bless you." Looking back at this season, that is the only phrase that fits. I am eternally grateful to have stood shoulder-to-shoulder with these giants of faith. They taught me that when we build God’s house, He builds us.