የጉልበት አስራት፡ በፈላ ዘይት ፊት የተገኘ በረከት
A moving reflection on the physical toll and spiritual rewards of service—honoring the "tattoos of service" earned at the stadium fryers.
VOLUNTEER EXPERIENCE
ጸሐፊ: ጋሽ ተሰማ
2/6/20262 min read
እውነት ነው፣ ዕድሜዬ ገፋ ብሏል። ነገር ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በዚያ የፈላ ዘይት ፊት ለፊት ቆሜ ሳገለግል፣ ድካም የሚባል ነገር ተሰምቶኝ አያውቅም። እግዚአብሔር ልዩ ጉልበት ሰጥቶኛልና።
የእኔ የምደባ ቦታ "ፍሬንች ፍራይስ" (French Fries) እና "ቺከን ቴንደር" (Chicken Tender) መጥበስ ነበር። ይህንን ስራ ከዚህ በፊት ሰርቼው አላውቅም፤ አብዛኞቻችንም እንደዛው። ነገር ግን በዚያ ሙቀትና ግርግር ውስጥ መንገዱን ተማርነው። ስታዲየሙ በደጋፊዎች ጩኸት፣ በመጠጥ እና በጨዋታ ሲናወጥ፣ እኛ በኩሽና ውስጥ ሆነን ዓይናችንን የትከልነው በአንድ ዓላማ ላይ ብቻ ነበር። እኛ ወደዚያ የሄድነው ጨዋታ ለመመልከት አልነበረም፤ የቅዱስ አማኑኤልን ደጆች ክፍት ለማድረግ እንጂ።
የተራበ አገልጋይ፣ የጠገበ መንፈስ
እኔን በጣም ያስደነቀኝ ነገር ቢኖር የአገልጋዮቹ መንፈሳዊ ጥንካሬ ነው። እስቲ አስቡት... በጾም ወቅት፣ የሥጋ መዓዛው አፍንጫን እየወጋ፣ ሆድ ባዶ ሆኖ ለሰዓታት ምግብ ማብሰል እንዴት ከባድ ነው። ነገር ግን ወጣቱም ሽማግሌውም፣ በጾም ቀን ስጋውን እየጠበሱ፣ ራሳቸው ሳይቀምሱ ለደንበኛ በፈገግታ ሲያቀርቡ ተመለከትኩ። "ዘይቱ የሥጋ ነካሽ ይኖረዋል" በሚል ጥንቃቄ፣ ድንቹን (Fries) እንኳን ከመብላት የተቆጠቡ ጽኑ ክርስቲያኖችን አየሁ። ስጋን ለቤተክርስቲያን ሲሉ መራብ—ይህ ከሰው የሚገኝ ኃይል አይደለም፤ ከእግዚአብሔር እንጂ።
የአገልግሎት "ታቱ" (Tattoo)
ይህ ጉዞ አልጋ በአልጋ አልነበረም። በዚያ መጥፎ የአየር ንብረት፣ በብርድና በሙቀት ውስጥ ለ30 ደቂቃ በእግር እንጓዝ ነበር። አውቶቡስ ለመጠበቅ በሰልፍ እንቆም ነበር። በኩሽናው ውስጥም አደጋ አለ። እኔ በራሴ ጣቶች ላይ የቃጠሎ ጠባሳ አለብኝ። ሌሎችም እጃቸውና እግራቸው ላይ ሲቃጠሉ አይቻለሁ። አንዳንዴም እርስ በርስ ሳንፈልግ የምንቃጠልበት ጊዜ ነበር። ነገር ግን እነዚህን ጠባሳዎች የምናያቸው እንደ ጉዳት ሳይሆን፣ እንደ "የአገልግሎት ምልክቶች" ነው። ሰማዕታት ስለ እምነታቸው ጠባሳ እንደኖረባቸው ሁሉ፣ እኛም ለዚህ ቅዱስ ቤት ስለደከምን የቃጠሎ ምልክቱን በፍቅር እንቀበለዋለን።
የቅዱስ ቁጣ ተአምር
የዘንድሮው አገልግሎት አንድ የሚገርም ነገር ነበረው። የተሰጠን የሽያጭ ቦታ (Store) ከባለፈው ዓመት ያነሰ ገቢ የሚያስገኝ ቦታ ነበር። በሰው ሎጂክ፣ የዘንድሮው ገቢ መቀነስ ነበረበት። ነገር ግን አገልጋዮቹ ይህንን ሲሰሙ ተስፋ አልቆረጡም። እንዲያውም አንድ ዓይነት "ቅዱስ ቁጣ" (Positive Anger) ተሰማቸው። ይህ መንፈሳዊ ቆራጥነት፣ ዝቅተኛ ቦታዎችን ወደ ወርቅ ማዕድን ቀየራቸው። በልዩ ተነሳሽነት በመስራት፣ የተሻለ ቦታ ከነበረን ጊዜ በላይ የላቀ ገቢ አገኘን።
የጉልበት አስራት
ሰዎች "እንዴት በዚህ ዕድሜ ለ16 ሰዓታት ትቆማለህ?" ብለው ይጠይቁኛል። መልሴ ቀላል ነው። ይህ "የጉልበት አስራት" ነው። ለዚህች ሟች ለሆነች ዓለም ለ16 ሰዓታት እንደክማለን። ታዲያ ለዘላለም ቤታችን፣ ለነፍሳችን መዳኛ ለሆነው ለቅዱስ አማኑኤል የአስራት ጉልበት ብንሰጥ ይበዛብናልን?
ይህ የባልቲሞር አገልግሎት ለቤተክርስቲያናችን የሕይወት መስመር (Lifeline) ነው። ከምእመናን የሚሰበሰበው ወርሃዊ መዋጮ ብቻውን ቤተክርስቲያኑን ማቆም እንደማይችል አውቃለሁ። ይህንን ሳስብ፣ ድካሙ "ስራ" ሳይሆን "ክብር" ይሆንብኛል።
በእሳት የተፈተነ ፍቅር
ይህንን መርከብ የመሩትን—ያሬድን፣ እዮብን፣ ክንዴን፣ ሰለሞንን፣ ቁምላቸውን፣ አሰገደችን እና የሎጂስቲክስ ቡድኑን—እግዚአብሔር ያክብርልን። በቤታችሁ ያላችሁ ልጆቼ ሆይ... አገልግሎትን አትፍሩት። ቤታችሁ እና ልጆቻችሁ የሚባረኩት በእናንተ ላብ ነው። እኛ በዚያ ኩሽና ውስጥ አብረን ሳቅን፣ አብረን ተቃጠልን፣ አብረን ጸለይን። ከማኅበራዊ ኑሮ በላይ የሆነ እውነተኛ ፍቅር ገንብተናል።
እመኑኝ፣ እኔ ለአንድም ቀን ድካም ተሰምቶኝ አያውቅም። ምክንያቱም ጉልበቱ የእግዚአብሔር እንጂ የእኔ አልነበረምና። ክብር ኃይል ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር ይሁን።
The Tithe of Sweat: A Blessing Found Before the Boiling Oil
It is true that I am one of the oldest volunteers, but for the last two years, standing in front of that boiling oil, I have never felt younger.
My station was specific: French fries and Chicken Tenders. I had no prior training in a commercial kitchen; none of us did. We figured it out through the heat and the chaos. While the stadium roared with fans cheering for their teams, drinking, and celebrating the world, we were tucked away in the kitchen, eyes fixed on a different goal. We weren't there to watch the game. We were there to keep the doors of St. Amanuel open.
The Fasting of the Cook
The most amazing thing I witnessed wasn't the crowd; it was the discipline of my fellow volunteers. Imagine cooking savory food for hours, the smell filling your lungs, while your stomach is empty. During fasting seasons, I watched young and old volunteers cook meat and serve customers with a smile, while strictly abstaining themselves. We didn't even taste the French fries, fearing they might have been fried in the same oil as the chicken. To starve the body while feeding the multitude—that is a strength that does not come from man. It comes only from God.
Scars of Honor
This work was not without its price. We walked thirty minutes in freezing winds and scorching heat just to get to the stadium. We waited in long lines for buses, shivering but standing together. And yes, there were accidents. In the rush of the kitchen, burns happen. I carry burns on my own fingers. I have seen others with scars on their hands and legs. But we do not look at these burns with regret. We look at them as "tattoos of service." Just as the martyrs bore the marks of their faith, we bear the small marks of our labor for His house.
The Miracle of "Holy Anger"
There is an irony to this year’s success. We were given locations that generated less income than the previous year. By all worldly logic, we should have failed. But when the volunteers heard we lost the "good stores," something shifted. We didn't get discouraged; we got "positively angry." That spiritual determination turned bad locations into gold mines. We worked harder, faster, and with more spirit, ultimately raising more money than when we had the better stores.
The Tithe of Labor (Asrat)
People ask why an elder would work hours in such conditions. My answer is simple: This is my Asrat (Tithe) of Labor. We toil 16 hours a day for our worldly lives, lives we will eventually walk away from. Is it then a burden to give a few hours for the House of God, which is our eternal home?
Without this Baltimore lifeline, our church would struggle to survive. Monthly contributions alone cannot sustain the sanctuary. Knowing this, I don't call this "work"; I call it "service." I call it a privilege.
A Family Forged in Fire
To those who led us—Yared, Eyob, Kinde, Solomon, Kumelachew, Asegedech, and the logistics team—thank you for guiding us. And to those sitting at home, I say this: Do not fear the labor. Your house and your children are blessed through your sweat. In that kitchen, we laughed together, burned together, and prayed together. We built a love that is stronger than any social club.
I never felt tired. Not once. Because the energy did not belong to Tessema. It belonged to God.